ደደቢት ላይ ቅጣት ተላለፈ

በ24ኛው ሳምንት የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ሶዶ ላይ ወላይታ ድቻ ከ ደደቢት ሊያደርጉት የነበረው ጨዋታ ደደቢት ሳይገኝ በመቅረቱ ፌዴሬሽኑ በደደቢት ላይ የቅጣት ውሳኔ አስተላልፏል።

ፌዴሬሽኑ ባስተላለፈው የዲሲፕሊን ውሳኔ ደደቢት በጨዋታው ባለመገኘቱ ለወላይታ ድቻ ከተሰጠው ፎርፌ (3 ነጥብ እና 3 ጎል) በተጨማሪ 60,000 ብር የገንዘብ ቅጣት ጥሎበታል። ከዚህ በተጨማሪም በእለቱ ሊገኝ የሚችለው የሜዳ ገቢ በሚቀርብ ማስረጃ ተሰልቶ ካሳ እንዲከፍል እና የክለቡ የቡድን መሪ ለ6 ወራት ከማንኛውም እንቅስቃሴ እንዲታገዱ መወሰኑን አስታውቋል።

ደደቢት በ23ኛው ሳምንት ከፋሲል ከነማ ጋር በተደረገው ጨዋታ በተከሰተው የስፖርታዊ ጨዋነት ጥሰት 150 ሺህ ብር እና ሁለት የሜዳው ጨዋታዎቹን በዝግ እንዲያደርግ ቅጣት እንደተጣለበት ይታወሳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡