ከፍተኛ ሊግ ለ | ወልቂጤ ከተማ ልዩነቱን የሚያሰፋበትን እድል ሳይጠቀምበት ቀርቷል

ወደ ዲላ ያመራው የምድብ ለ መሪ ወልቂጤ ከተማ በባለፈው ሳምንት ከዲላ ጋር የመጀመሪያውን አጋማሽ አከናውኖ በዝናብ ምክንያት መቋረጡ የሚታወስ ነው። በዚህም የምድቡ 19ኛ ሳምንት ሳይከናወኑ የተቀቀረጠው ጨዋታ እንዲቀጥል በተወሰነው ውሳኔ መሰረት እሁድ ረፋድ ዲላ ላይ ቀጥሎ 2-2 ተጠናቋል።

ጨዋታው ከመቋረጡ በፊት 1-1 የነበረ ሲሆን ዲላ በቢንያም በቀለ የ16ኛው ደቂቃ ጎል መሪ ሆኖ ሐብታሙ ታደሰ በ20ው ደቂቃ ወልቂጤን አቻ አድርጎ ነበር የተቋረጠው። በእሁዱ ጨዋታ አህመድ ሁሴን በ50ኛው ደቂቃ ወልቂጤን መሪ ማድረግ ችሎ የነበረ ቢሆንም ኋላ ላይ በራሳቸው ላይ በተቆጠረ ግብ አቻ 2-2 ወጥተዋል።

ውጤቱን ተከትሎ ሊጠናቀቅ አራት ጨዋታዎች ብቻ በሚቀሩት ምድብ ለ ወልቂጤ ከተማ 39 ነጥብ በመስበስብ ከተከታዩ መድን በሶስት ነጥብ ልዩነት እየመራ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡