ሀሌታ የታዳጊዎች ቡድን በስዊድን የታዳጊዎች ውድድር ላይ እየተሳተፈ ይገኛል

በስዊድን ጉተንበርግ ከተማ የሚከናወነው ዓመታዊው የጎቲያ የታዳጊዎች ውድድር ካሳለፍነው ሰኞ ጀምሮ እየተከናወነ የሚገኝ ሲሆን የሀሌታ ከ12 ዓመት በታች ቡድን ዛሬ የመጨረሻ ጨዋታውን አከናውኗል።

ከ75 ሀገራት የተውጣጡ 1686 ቡድኖች የሚሳተፉበት ይህ ውድድር በሁለቱም ፆታ በተለያዩ የዕድሜ እርከኖች የሚከናወን ሲሆን የ12 ዓመት በታች ውድድር በ40 ምድቦች ተከፍሎ እየተከናወነ ይገኛል። እያንዳንዱ ቡድን በየቀኑ አንድ ጨዋታ (አንዱ ጨዋታ 40 ደቂቃ ይፈጃል) የሚያከናውን ሲሆን በአሰልጣኝ ዐቢይ ካሳሁን የሚመራው ሀሌታ ቡድንም ከስዊድኖቹ ሀስለሆልምስ እና ሊዲንጎ እንዲሁም እንግሊዙ ላየን ብሉ ጋር በምድብ 18 ላይ ባደረጋቸው ሦስት ጨዋታዎች ሽንፈት አስተናግዷል ።

በዚህ ዓመታዊ የታዳጊዎች ውድድር ላይ ከዚህ ቀደምም አሴጋ አካዳሚ እና ፓሽን አካዳሚን የመሳሰሉ ቡድኖች ተሳትፎ ማድረጋቸው ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡