ሀዲያ ሆሳዕና የቀድሞ ተጫዋቹን መልሷል

ከከፍተኛ ሊግ ካደጉ ክለቦች መካከል አንዱ የሆነው ሀዲያ ሆሳዕና ሄኖክ አርፊጮን ከአንድ ዓመት በኋላ ወደ ቡድኑ መልሷል።

የግራ መስመር ተከላካዩ ሄኖክ በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት ሆሳዕናን በመልቀቅ በወላይታ ድቻ ቆይታ ያደረገ ሲሆን ዳግም ለሁለተኛ ጊዜ ከቀድሞው አሰልጣኙ ጋር ያገናኘውን ዝውውር በማጠናቀቅ ወደ ክለቡ መቀላቀል ችሏል፡፡ የቀድሞ የቡድኑ አምበል ለአንድ ዓመት ውል ነው ነብሮቹን የተቀላቀለው።

ሆሳዕና ከሄኖክ በተጨማሪ እስካሁን የአሰልጣኙ ግርማ ታደሰን ውል ለተጨማሪ አንድ ዓመት ሲያድስ ደስታ ጊቻሞ፣ ብሩክ ኤልያስ እና አብዱልሰመድ ዓሊን ወደ ክለቡ አምጥቷል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡