የካፍ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ የተጫዋቾችን የማስመዝገቢያ ጊዜ አብቅቷል

የአፍሪካ እግርኳስ ኮንፌድሬሽን (ካፍ) ከሚያዘጋጃቸው ውድድሮች መካከል በክለቦች ደረጃ የሚካሄደው የአፍሪካ ቻምፒየንስ ሊግ እና ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ይጠቀሳሉ፡፡ በሁለቱ ውድድሮች ላይ የሚሳተፉ ክለቦች ተጫዋቾቻቸውን የማስመዝገቢያ ቀነገደብ ዓርብ ጥር 15 2016 ተጠናቅቋል፡፡ የተጫዋቾችን የማስመዝገቢያ ቀነገደቡ ከታህሳስ 31 2015 የተራዘመ ነበር፡፡

ኢትዮጵያን ወክለው በውድድሮቹ ላይ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና መከላከያ ይሳተፋሉ፡፡ ቅዱስ ጊዮርጊስ በቻምፒየንስ ሊግ ቅድመ ማጣሪያ ከሲሸልሱ ባርክሌይ ሊግ ሻምፒዮን ሴንት ሚካኤል ይጫወታል፡፡ በኮንፌድሬሽን ዋንጫ መከላከያ በግብፅ ፕሪምየር ሊግ አስገራሚ የውድድር ዘመን እያሰላፈ የሚገኘውን ምስር አል ማቃሳን ይገጥማል፡፡ ምስር አል ማቃሳ የግብፅ ፕሪምየር ሊግን በ27 ነጥብ ይመራል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *