ቅዱስ ጊዮርጊስ ወደ ሃዋሳ?

የ2007 የፕሪሚየር ሊጉ ቻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ በቀጣዩ ወር የሚደረገውን የቻምፒዮንስ ሊግ ቅድመ ማጣርያ ጨዋታ በሀዋሳ ለማካሄድ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

ክለቡ ከሲሸልሱ ቻምፒዮን ሴይንት ሚቼል ጋር የሚያደርገውን ጨዋታ በሀዋሳ ማካሄድ እንደሚፈልግ ለፌዴሬሽኑ ያሳወቀ ሲሆን የካፍ ሃላፊዎችም የስታድየሙን ብቁነት ገምግመው ውሳኔ ያሳልፋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡

ፈረሰኞቹ አምና ከአልጄርያው ኤምሲ ኡልማ ጋር ያደረጉትን ጨዋታ በባህር ዳር ስታድየም አካሂደው ከ65 ሺህ በላይ ተመልካች በማስተናገድ በኢትዮጵያ እግርኳስ ታሪክ በርካታ ህዝብ በስታድየም ከተከታተላቸው ጨዋታዎች አንዱ መሆን ችሎ እንደነበር ይታወሳል፡፡

በመጠናቀቅ ላይ የሚገኘው የሀዋሳ ስታድየም ዘንድሮ ኢትዮጵያ ባስተናገደችው ሴካፋ ላይ የምድብ ጨዋታዎችን በማስተናገድ የኢንተርናሽናል ጨዋታዎችን የማስተናገድ ልምድ አካብቷል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *