የ2018 ቻን እንድታስተናግድ ተመርጣ የነበረችው ኬንያ ውድድሩን የማስተናገድ ብቃቷ ጥያቄ ምልክት ውስጥ መግባቱን ተከትሎ በ2020 ልታስተናግድ የተመረጠችው ኢትዮጵያ ከታሰበው 2 አመት ቀድማ የአፍሪካ ሃገራት ዋንጫን ልታስተናግድ እንደምትችል ከፌዴሬሽኑ የሚወጡ መረጃዎች አመልክተዋል፡፡
ኬንያ በጋሪሳ ያስተናገደችው የሽብር ጥቃት እና ተከትሎ የመጣው ተጨማሪ የፀጥታ ስጋት እንዲሁም የገንዘብ አቅም እና ደረጃቸውን የጠበቁ ስታድየሞች በበቂ ሁኔታ አለመኖር ውድድሩ በምስራቅ አፍሪካዊቷ ሃገር መከሄዱን ጥያቄ አጭሮበታል፡፡
በ2020 ቻንን እንድታስተናግድ የተመረጠችው ኢትዮጵያ በሀዋሳ ፣ መቐለ ፣ ወልድያ ፣ ነቀምት ፣ ጋምቤላ እና ባህርዳር ሊጠናቀቁ የተቃረቡ ስታድየሞችን የገነባች ሲሆን በአዳማ ፣ ድሬዳዋ እና አዲስ አበባ አዳዲስ ስታድየሞችን ለመገንባት የዲዛይን ስራዎች ተጠናቀዋል፡፡