ኢትዮጵያዊው አጥቂ ኡመድ ኡኩሪ ክለቡ ኢኤንፒፒኤይ ታላል ኤል ጋይሽን ከሜዳው ውጪ በካይሮ ሚሊተሪ ስታዲየም 3-1 ባሸነፈበት ጨዋታ የግብፅ ፕሪምርሊግ ጨዋታ በቡድኑ ውስት ሳይካተት ቀርቷል፡፡ ለኢኤንፒፒኤ ግቦቹን ራሚ ሳብሪ፣ ሳላ ሱሌማን እና ኑር ኤል ሰዒድ አስቆጥረዋል፡፡ ኤልጋይሽን ከባዶ መሸነፍ ያደነች ግብ መሃሙድ ሪዚክ ባድር በስሙ አስመዝግቧል፡፡
ከአሰልጣኝ ሃኒ ራምዚ ጋር ባሳለፍነው ሳምንት የተለያየው ኢኤንፒፒአይ ኡመድን በነፃ ዝውውር ያስፈረመው በዓመቱ መጀመሪያ ነበር፡፡ ኡመድ ያለፉትን ሁለት ተከታታይ የሊግ ጨዋታዎች አምልጠውታል፡፡
ኢኤንፒፒአይ 18 ክለቦች በሚሳተፉበት የግብፅ ፕሪምየርሊግ በ17 ነጥብ 10ኛ ነው፡፡ ክለቡ በካፍ ኮንፌድሬሽን ዋንጫ ላይም ተሳታፊ ይሆናል፡፡ ኢኤንፒፒኤይ በሁለተኛው ዙር የኮትዲቯሩን አፍሪካ ስፖርት እና የኮንጎ ብራዛቪሉን ዲያብልስ ኖሪስን አሸናፊ ይገጥማል፡፡