ሰበር ዜና| የኢትዮጵያ ተጫዋቾች ደሞዝ ጣርያ እንዲበጅለት ተወሰነ

በተጫዋቾች ደሞዝ እና ተያያዥ ጉዳዮች ዙርያ ዛሬ በቢሾፍቱ የምክክር መድረክ እየተከናወነ ይገኛል። በመድረኩም የተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያ እንዲበጅለት ከስምምነት ተደርሷል።

በመድረኩ ከደደቢት፣ ሽረ፣ ወልዋሎ፣ ቅዱስ ጊዮርጊስ እና ኢትዮጵያ ቡና በቀር ሌሎች 13 የፕሪምየር ሊጉ ክለቦች የተገኙ ሲሆን የተጫዋቾች የደሞዝ ጣርያ እንዲኖር በአብላጫ ውሳኔ ከተወሰነ በኋላ 10 ክለቦች የአንድ ተጫዋች ከፍተኛ ወርሀዊ ደሞዝ 50,000 ብር እንዲሆን ተስማምተዋል።

ይህ የደሞዝ ጣርያ ከዛሬ ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ የተገለፀ ሲሆን በክረምቱ የፈረሙ አዲስ ተጫዋቾችም ሆኑ ከዚህ ቀደም ውል የነበራቸው ተጫዋቾች በውል ማፍረሻ ላይ በተቀመጠው ህግ መሠረት እንዲቋረጥ ተደርጎ ወደተጠቀመጠው አዲስ ደንብ ይሸጋሸጋል ተብሏል።

ተጨማሪ ዝርዝር ውሳኔዎች እና ስብሰባውን የተመለከቱ መረጃዎች ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡