የእሁዱ የፋሲል ከነማ ጨዋታ የቴሌቪዥን ሽፋን ያገኛል

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ፋሲል ከነማ ከታንዛንያው አዛም ጋር የሚያደርገው ጨዋታ የቀጥታ የቴሌቪዥን ስርጭት እንደሚያገኝ ታውቋል።

ሃዋሳ ከተማን በመለያ ምት በማሸነፍ ወደ አህጉራዊ ውድድሮች በታሪካቸው ለመጀመሪያ ጊዜ ያመሩት ፋሲል ከነማዎች እሁድ ከታንዛኒያው ክለብ አዛም ጋር የመጀመሪያ የማጣሪያ ጨዋታቸውን ያደርጋሉ። በባህር ዳር ዓለምአቀፍ ስታዲየም የሚደረገው ይህ ጨዋታም በአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት (አማራ ቲቪ) በቀጥታ እንደሚተላለፍ ታውቋል። ከተቋሙ ባገኘነው መረጃ መሰረት ጨዋታውን ለማስተላለፍ ስራዎች እየተሰሩ መሆናቸው ሲገለፅ መቀመጫውን ታንዛኒያ ያደረገው አዛም ቲቪም ከቴሌቪዥን ጣቢያው (አማራ ቲቪ) ጋር ተስማምቶ ጨዋታውን ለማስተላለፍ እንደተወሰነ እና መከፈል ያለበትን ክፍያ ለጣቢያው እንደፈፀመ ተነግሯል።

በተያያዘ ዜና ጨዋታውን የሚመሩት ሱዳናዊው ዳኞች ባህር ዳር መግባታቸው ተረጋግጣል። ሶከር ኢትዮጵያም ጨዋታውን በቀጥታ የፅሁፍ ስርጭት ለስፖርት ቤተሰቡ እንደሚያደርስ ለማሳወቅ ይወዳል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡