ገናናው ረጋሳ ወደ ወልዋሎ አምርቷል

እንደ አዲስ ቡድናቸውን በማዋቀር ላይ የሚገኙት ቢጫ ለባሾቹ ከዚ ቀደም ከድሬዳዋ ከተማ ሦስት ተጫዋቾች ያስፈረሙ ሲሆን ዛሬ ደግሞ አራተኛውን በእጃቸው አስገብተዋል።

በተለያዩ ቦታዎች ላይ መጫወት የሚችለው ገናናው ረጋሳ ወደ ወልዋሎ ያመራ ተጫዋች ነው። ባለፈው ዓመት ጋር በድሬዳዋ ድንቅ ጊዜ ያሳለፈው ገናናው በመስመር ተከላካይነት እንደመጫወቱ ወደ ፋሲል ከነማ ያመራው እንየው ካሳሁን ሁነኛ ተተኪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

ወልዋሎዎች ተጫዋቹን እስከ ውድድር ዓመቱ መጨረሻ ከቡድናቸው ጋር እንዲቆይ ያስፈረሙት ሲሆን በድጋሚ ከአሰልጣኝ ዮሃንስ ሳህሌ ጋር የመገናኘት ዕድልም አግኝቷል።

ዘጠኝ አዲስ ተጫዋች ያስፈረሙት ቢጫ ለባሾቹ ከዚ በኋላ ወደ ነባር ተጫዋቾች ውል ማራዘም ፊታቸው ያዞራሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡