ወልዋሎ ሁለት ተጫዋቾችን ከከፍተኛ ሊግ አስፈረመ

ባለፉት ዓመታት ቡድናቸው ካገለገሉት እና ውላቸውን ካጠናቀቁት ተጫዋቾች ጋር እየተለያዩ የሚገኙት ቢጫ ለባሾቹ ከኢትዮጵያ መድን ሁለት ተጫዋቾች በማስፈረም የአዳዲስ ተጫዋቾችን ቁጥር ስምንት አድርሰዋል።

ምስጋናው ወልደዮሐንስ ወደ ወልዋሎ ካመሩት መካከል ነው። የመስመር ተጫዋቹ በደቡብ ፖሊስ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዋሳ ከተማ የተጫወተ ሲሆን በዘንድሮው የውድድር ዘመን ከመድን ጋር ጥሩ ጊዜ ማሳለፍ ችሏል።

ጀሚል ያዕቆብ ሌላው ክለቡን የተቀላቀለ ተጫዋች ነው። ጀሚል ጅማ አባ ቡናን ከለቀቀ በኋላ ለኢትዮጵያ መድን ሲጫወት የቆየ ሲሆን በመስመር ተከላካይ ቦታ ላይ ጥሩ ተፎካካሪ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።

የዛሬውን ጨምሮ ለወልዋሎ በአጠቃላይ ከፈረሙት ስምንት ተጫዋቾችን አራቱ የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በመድን ያሳለፉ ነበሩ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡