ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ነገ የኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ጨዋታን ይመራሉ

በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ነገ ከሚደረጉ ጨዋታዎች መካከል ጅቡቲ ላይ የሚደረገውን ጨዋታ አራት ኢትዮጵያዊያን ዳኞች ይመሩታል።

ነገ አመሻሽ 11:00 ላይ ጅቡቲ ላይ የጅቡቲው ክለብ አርታ ሶላር ሰቨን ከሱዳኑ አህሊ ካርቱም ጋር ጨዋታውን ሲያደርግ አራት ኢትዮጵያዊያን ኢንተርናሽናል ዳኞች ይህን ጨዋታ እንዲመሩ መመረጣቸውን ሶከር ኢትዮጵያ ያገኘችው መረጃ ይጠቁማል። በዋና ዳኝነት ለሚ ንጉሴ ሲመራው አብረውት ደግሞ በረዳትነት ኃይለራጉኤል ወልዳይ እና በላቸው ይታየው እንዲሁም ዳዊት አሳምነው በአራተኛ ዳኝነት የሚያጫወቱ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡