ሁለት የከፍተኛ ሊግ ክለቦች አሰልጣኝ ቀጥረዋል

ኢትዮጵያ መድን እና አክሱም ከተማ የአዲስ አሰልጣኝ ቅጥር ፈፅመዋል።

ባለፈው የውድድር ዓመት በምድብ ለ ተፎካካሪ የነበረው ኢትዮጵያ መድን አሰልጣኝ በፀሎት ልዑልሰገድ ጋር ከተለያየ በኋላ ምክትላቸው አሰልጣኝ ያሬድ ቶሌራ መቅጠሩን አሳውቋል። አሰልጣኝ ያሬድ ከዚህ በፊት በለገጣፎ፣ ወልቂጤ፣ የኢትዮጵያ መድን ተስፋ ቡድን፣ በኢትዮጵያ ሴቶች ብሔራዊ ቡድን እንዲሁም በኢትዮጵያ ከ17 ዓመት በታች ብሔራዊ ቡድን አሰልጣኝ ሆነው አገልግለዋል። በ2012 የቀድሞ ቡድናቸውን በዋና አሰልጣኝነት ይዘው የሚቀጥሉም ይሆናል።

አክሱም ከተማ ከአሰልጣኝ ጌታቸው ጋር ከተለያየ በኋላ አሰልጣኝ ፍለጋ ላይ ቆይቶ አሰልጣኝ ዳንኤል ፀሀዬን ቀጥረው ስራቸውን ጀምረዋል። አሰልጣኝ ዳንኤል ከደደቢት ተስፋ እንዲሁም ዋና ቡድን፤ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ምክትል አሰልጣኝ፣ የስሑል ሽረ ቡድን ያሰለጠኗቸው ቡድኖች ናቸው። ስሑል ሽረ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግ ዋና አሰልጣኝ የነበሩ ሲሆን ከውድድር ዓመቱ አጋማሽ ጀምሮ ደደቢትን ሲመሩ ቆይተዋል።

በተያያዘ ዜና ደግአረግ ይግዛውን የሚተካ አሰልጣኝ እየፈለገ የሚገኘው ኢኮስኮ የአሰልጣኞች ቅጥር ማስታወቂያ አውጥቶ የመጨረሻ ሦስት እጩዎችን በመለየት ለቃል ፈተና ጠርቷል። በፀሎት ልዑልሰገድ፣ አስራት አባተ እና ታዬ የመጨረሻዎቹ እጩዎች ሲሆኑ ሶከር ኢትዮጵያ ባገኘችው መረጃ ክለቡ በዚህ ሁለት ቀን ውስጥ አሰልጣኝ ቅጥሩን ያሳውቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡