ፍሊፕ ኦቮኖ የብሄራዊ ቡድን ጥሪ ደረሰው

የመቐለ 70 እንደርታው ኢኳቶሪያል ጊንያዊ ግብጠባቂ ፍሊፕ ኦቮኖ ምባንግ ከብሔራዊ ቡድኑ ጥሪ ደረሶታል።

ባለፈው ዓመት መቐለ 70 እንደርታ ዋንጫ እንዲያነሱ ጉልህ ሚና ከነበራቸው ተጫዋቾች ስሙ በግንባር ቀደምትነት የሚጠቀሰው ግብ ጠባቂው ሃገሩ ከደቡብ ሱዳን ጋር ላለባት የዓለም ዋንጫ ማጣርያ ዝግጅት ነው ጥሪ የደረሰው።

ገና በአስራ ስድስት ዓመቱ ለዋናው የሃገሩን ብሄራዊ ቡድን መጫወት የጀመረው ግብጠባቂው ሃገሩን በሁለት የአፍሪካ ዋንጫዎች የወከለ ሲሆን ቡድኑን በአምበልነት እስከመምራትም ደርሷል። ባለፈው ዓመት መጀመርያ ወደ ኢትዮጵያ መጥቶ ምዓም አናብስት በመቀላቀል በሁለቱም ዓመት ምርጥ ብቃት በማሳየት በቀላሉ በደጋፊዎች ልብ የገባ ሲሆን በትውልድ አከባቢውም ጥሩ ተቀባይነት እንዳለው ይነገርለታል። ባለፈው ሳምንት የትውልድ ከተማው ሞንጎሞ ተወላጆች ወደ ማላቦ በማቅናት መቐለ 70 እንደርታ ከ ካኖ ስፖርትስ አካዳሚ ያደረጉትን ጨዋታ ለሱ እና ለቡድኑ ያደረጉላቸው አቀባበል ለዚ ማሳያ ነው።

እንደሚታወሰው የፍሊፕ ኦቮኖ ታናሽ ወንድም ፓስካስዮስ ኦቮኖ የሀዲያ ሆሳዕና ግብጠባቂ ሲሆን ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ ሲያድግም ጥሩ አስተዋጽኦ ካደረጉት ተጫዋቾች አንዱ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡