ሀዲያ ሆሳዕና ሦስት ተጫዋቾች አስፈረመ

ወደ ፕሪምየር ሊጉ የተመለሰው ሀዲያ ሆሳዕና ሦስት አዳዲስ ተጫዋቾችን ማስፈረሙን አስታውቋል።
ሆሳዕና ካስፈረማቸው መካከል ሁለቱ ተጫዋቾች ዓመቱን በከፍተኛ ሊግ ለአርባምንጭ በመጫወት ያሳለፉትና ከዚህ ቀደም የክለቡ ተጫዋቾች የነበሩት የመስመር ተጫዋቹ መስቀሉ ለቴቦ እና ተከላካዩ በረከት ወልደዮሀንስ ናቸው።

ሌላው ክለቡን የተቀላቀለው የመስመር ተጫዋቹ ሱራፌል ዳንኤል ነው። በመስመር ተከላካይነት እና አጥቂነት መጫወት የሚችለው ሱራፌል ድሬዳዋ ከተማን ከለቀቀ በኋላ በ2011 ለአዳማ ከተማ በመጫወት ማሳለፉ ይታወሳል።

ከሦስቱ ፈራሚዎች በፊት ሄኖክ አርፊጮ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ አብዱሰመድ ዓሊ፣ ብሩክ ኤልያስ እና ይሁን እንዳሻውን ወደ ቡድኑ የቀላቀለው ሀዲያ ሆሳዕና የአሰልጣኝ ግርማ ታደሰን ውል ማራዘሙ የሚታወስ ሲሆን የስምንት ተጫዋቾች ውል መታደሱንም ለማወቅ ተችሏል። ከነዚህም መካከል ቡድኑ ወደ ፕሪምየር ሊግ እንዲያድግ ቁልፍ ሚና የተወጡት ትዕግስቱ አበራ፣ ሱራፌል ጌታቸው፣ ዮሴፍ ደንገቱ ፣ ፍራኦል መንግስቱ እና እዮኤል ሳሙኤል ይጠቀሳሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡