ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን የመጀመርያ ጉባዔውን ያካሂዳል

ኢትዮጵያን ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በወቅታዊ ጉዳይ አስመልክቶ ከአባላቶቹ ጋር ውይይት ሊያደርግ ነው።

ከሳምንታት በፊት የተመሰረተው የኢትዮጵያ ፕሮፌሽናል ፉትቦለርስ አሶሴሽን በመጪው ሐሙስ ነሐሴ 16 በዋቤሸበሌ ሆቴል 3:00 በሚያደርገው የመጀመርያ ስብሰባው በወቅታዊ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ውይይት ያደርጋል ተብሎ ሲጠበቅ በተለይም ከሰሞኑ ፌዴሬሽኑ ያደቀው የደሞዝ ጣርያ ውሳኔ ሰፊ የመወያያ አጀንዳ እንደሚሆን ይጠበቃል።

በሃገሪቱ የሚገኙት የእግር ኳስ ተጫዋቾች በጉባዔው ላይ እንዲገኙ ጥሪ ያቀረበው ማኅበሩ ከሐሙሱ ጉባዔ በኋላ በሚኖሩ ቀናት መግለጫ እንደሚሰጥም ለማወቅ ተችሏል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡