ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ| በዛብህ መለዮ ከመልሱ ጨዋታ ውጪ ሆነ

ዐፄዎች በካፍ ኮንፌዴሬሽን ዋንጫ ቀድመ ማጣርያ የመልስ ጨዋታ የበዛብህ መለዮን ግልጋሎት እንደማያገኙ ተረጋግጧል።

ፋሲሎች ሜዳቸው ከአዛም ጋር ያደረጉትን ጨዋታ 1-0 ሲያሸንፉ በጨዋታው ላይ ጉልህ ድርሻ የነበረው እና ብቸኛዋን ግብ ያስቆጠረው በዛብህ መለዮ ያጋጠመው ቀለል ያለ የዲስክ መንሸራተት ህመም ሲሆን ከቡድኑ ፊዚዮትራፒስት ሽመልስ ደሳለኝ ባገኘነው መረጃ በህክምናው አገላለፅ <LS disc protrusion> የሚባል ችግር ያጋጠመው በመሆኑ 10 ቀናት ከሜዳ የሚያርቀው ይሆናል።

በኮንፌዴሬሽን ዋንጫው ለሁለተኛ ጊዜ ተሳትፎ እያደረገ የሚገኘው በዛብህ መለዮ የፋሲልን የመጀመርያ ታሪካዊ ጎል ከማስቆጠሩ በተጨማሪ በ2018 ተመሳሳይ ውድድር የመጀመርያ ዙር ላይም በወላይታ ድቻ መለያ ዛማሌክ ላይ ጎል ማስቆጠሩ የሚታወስ ነው።

 


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡