ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ኤርትራ ሱዳንን ስትረመርም ኬንያ እና ብሩንዲ ነጥብ ተጋርተዋል

አምስተኛ ቀኑን የያዘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ዛሬም ሲቀጥል ኤርትራ ሱዳንን በሰፊ ውጤት አሸንፋ የማለፍ ዕድልዋ አለምልማለች። ኬንያ ደግሞ ከብሩንዲ ጋር ነጥብ ተጋርታለች።

በስምንት ሰዓት ጨዋታቸውን ያካሄዱት ኬንያ እና ብሩንዲ ሲሆኑ ኬንያ 1-0 እየመራች አመዛኙ የጨዋታው ደቂቃዎች ብትቆይም ብሩንዲ በጨዋታው መገባደጃ አከባቢ ግብ አስቆጥራ ከመሸነፍ ድናለች።

የዕለቱ ሁለተኛ ጨዋታ አዘጋጇ ኤርትራን ከ ሱዳን ያገናኘው ሲሆን በርካታ ተመልካችም ተከታትሎታል። በመጀመርያው ጨዋታዋ በደጋፊዋ ፊት ሽንፈት የገጠማት ኤርትራ ግጥሚያውን 6-0 በማሸነፍ ነጥቧን ወደ ሦስት አሳድጋ ወደ ግማሽ ፍፃሜ የማለፍ ተስፋዋን አለምልማለች። አሕመድ አውድ የተባለ ተጫዋች ሦስት ግቦች አስቆጥሮ ሐት-ትሪክ ሲሰራ ተመስገን ተስፋይ የተባለው የመስመር ተጫዋች ደግሞ አንድ ጎል አስቆጥሯል። የተቀሩት ሁለት ግቦች ተያ አሕመድ የተባለ የሱዳን ተከላካይ በራሱ ግብ ላይ የተቆጠሩ ናቸው።

ቡድን | ተጫወተ | ልዩነት |  ነጥብ

1) ኬንያ 3 (+6)   7

2) ብሩንዲ 3 (+2) 7

3) ኤርትራ 2 (+5) 3

4) ሶማልያ 2 (-3) 0

5) ሱዳን 2  (-10) 0

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል ደቡብ ሱዳን ከ ታንዛንያ በ8:00 ፣ ኢትዮጵያ ከሩዋንዳ በ10:30 ይጫወታሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡