ሴካፋ ከ15 ዓመት በታች| ሶማሊያ ስታሸንፍ ኤርትራ ከምድብ ተሰናብታለች

ሰባተኛ ቀኑን የያዘው የሴካፋ ከ15 ዓመት በታች ውድድር ዛሬም ሲቀጥል ሶማሊያ እና ኬንያ ተጋጣሚዎቻቸውን አሸንፈዋል። አዘጋጇ ኤርትራም ከምድብዋ ሳታልፍ ቀርታለች።

በ8:00 የተካሄደው የሶማሊያ እና ሱዳን ጨዋታ ሲሆን ሶማሊያ ከጨዋታ ብልጫ ጋር 2-0 አሸንፋለች። በጨዋታው የብዙዎች አድናቆት ለጎረፈላቸው ሶማሊያዎች ጎልቹ ያስቆጠሩት ሞሐመድ ዓብዱልቃድር እና አብዱላሂ ዑመር ናቸው።

ሁለተኛ የነበረው ጨዋታ የኤርትራ እና የውድድሩ ጠንካራ ቡድን ኬንያ ሲሆን ኬንያ አዘጋጅዋን 2-1 በማሸነፍ ምድቡን መርታ ወደ ቀጣዩ ዙር ማለፏ አረጋግጣለች። ኤርትራም በደጋፊዎችዋ ፊት ከምድቧ በመውደቅ አሳዛኝ ተሳናባች ሆናለች።

ውድድሩ ነገም ሲቀጥል በ8:00 ታንዛኒያ እና ሩዋንዳ በ10:30 ደግሞ ዩጋንዳ እና ደቡብ ሱዳን ይጫወታሉ። አስቀድማ ተሰናባች መሆኗን ያረጋገጠችው ኢትዮጵያ የዕለቱ አራፊ ቡድን ናት።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡