ከፍተኛ ሊግ| ዲላ ከተማ የአሰልጣኝ ቅጥር ፈፀመ

የከፍተኛ ሊጉ ክለብ ዲላ ከተማ በውድድሩ ልምድ ያላቸው አሰልጣኝ ደረጄ በላይን ቀጥረዋል።

በዓመቱ አጋማሽ ከአሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ ጋር ከተለያዩ በኋላ በምክትል አሰልጣኝ ሲመሩ የቆዩት ዲላ ከተማዎች አሰልጣኝ ደረጀ በላይን ከዚህ ቀደም ሦስት ቡድኖችን ወደ ፕሪምየር ሊግ በማሳደግ ታሪክ ያላቸው ደረጄ በላይን በአሰልጣኝኘት የሾሙ ሲሆን በ2000 በሰበታ ከተማ፣ በ2008 በጅማ አባ ቡና እንዲሁም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በወልቂጤ ከተማ ያሳኩትን ስኬት በዲላም የመድገም ሃላፊነት ተጥሎባቸዋል።

አሰልጣኝ ደረጀ በላይ ከሶከር ኢትዮጵያ ጋር በነበራቸው ቆይታ ጥሩ ጨዋታ የሚሳይ ውጤታማ ቡድን በመገንባት ወደ ፕሪምየር ሊግ ለማሳደግ ጠንክረው እንደሚሰሩ ተናግረዋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡