ሰበታ ከተማ ሦስተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

ወደ ዝውውር ገበያው ዘግይቶ ቢገባም በከፍተኛ ሁኔታ እየተንቀሳቀሰ የሚገኘው ሰበታ ከተማ የቀድሞ ተጫዋቹን ወደ ቡድኑ ለመመለስ ከስምምነት ደርሷል።

የአጥቂ አማካይ ስፍራ ላይ የሚጫወተውና የእግርኳስ ህይወቱን በክለብ ደረጃ ለሰበታ ከተማ በመጫወት የጀመረው አስራት ቱንጆ ጅማ አባ ጅፋርን (የቀድሞ ጅማ ከተማ) በመቀላቀል ወደ ኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ እንዲገቡ ከፍተኛውን አስተዋፅኦ ከተወጡ ተጫዋቾች መካከል አንዱ ነበር። በመቀጠል ለኢትዮጵያ ቡና ሁለት ዓመታትን በተለያዩ ቦታዎች ተሰልፎ በማገልገል ጥሩ ጊዜያትን ያሳለፈው አስራት አሁን ደግሞ ማረፊያው የቀድሞ ክለቡ ሰበታ ከተማ እንዲሆን ዛሬ ከስምምነት ደርሷል።

ከበኃይሉ አሰፋ እና አዲስ ተስፋዬ በመቀጠል ሦስተኛ ተጫዋቻቸውን ለማስፈረም ከስምምነት የደረሱት ሰበታዎች በቀጣዮቹ ቀናት ተጨማሪ ተጫዋቾችን ሊያስፈርሙ እንደሚችሉ እየተጠበቀ ይገኛል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡