ኢትዮጵያ ቡና ሦስተኛ ተጫዋቹን አስፈርሟል

ሁለት ተጫዋቾችን ቀደም ብሎ ወደ ክለቡ የቀላቀለው ኢትዮጵያ ቡና ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆን ለማስፈረም ከስምምነት ደርሷል።

የቀድሞው የሀላባ ከተማ እና አዲስ አበባ ከተማ ግብ ጠባቂው ተክለማርያም ሻንቆ ባለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት በሀዋሳ ከተማ ከቶጓዊው ግብ ጠባቂ ሶሆሆ ሜንሳህ ጋር እየተፈራረቀ የክለቡ ግብ የጠበቀ ሲሆን ዘንድሮም በተመሳሳይ በሀዋሳ ቆይታ ለማድረግ ተስማምቶ የነበረ ቢሆንም ስምምነቱን አፍርሶ ወደ ቡና ማምራቱ ታውቋል።

ዓለምአንተ ካሳ የክለቡ ቀዳሚ ፈራሚ ነው። የቀድሞው የወልዋሎ የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ወደ ደደቢት ከተመለሰ በኋላ ያለፉትን ሁለት የውድድር ዓመታት መጫወት ችሏል።

ሁለተኛው አዲስ ፈራሚ የሆነው የአጥቂ ስፍራ ተጫዋቹ ሰይፈ ዛኪር ነው። በፌዴራል ፖሊስ በተጠናቀቀው ዓመት በተለይም በሁለተኛው ዙር ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ያሳየው ይህ ወጣት አጥቂ ቡድኑ በከፍተኛ ሊጉ ከመውረድ እንዲተርፍ ያስቻሉ ወሳኝ ጎሎችን አስቆጥሯል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡