ባህር ዳር ከተማዎች ተጫዋች ማስፈረማቸውን ቀጥለዋል

የጣና ሞገዶቹ ዘግይተው ወደ ዝውውር እንቅስቃሴ በመግባት ተጫዋቾች በማስፈረም ላይ ሲገኙ በዛሬው ዕለትም አፈወርቅ ኃይሉን ወደ ቡድናቸው ቀላቅለዋል።

ታታሪው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች በወልዋሎ መልካም ጊዜያትን ያሳለፈ ሲሆን በተለይም በተጠናቀቀው የውድድር ዓመት በኢትዮጵያ የኦሊምፒክ እና ዋናው ብሔራዊ ቡድን ጥሪ እንዲደርሰው ያስቻለ እንቅስቃሴ ማድረግ ችሏል።

ባህር ዳር ከተማዎች በ1 ዓመት ኮንትራት ካስፈረመው አፈወርቅ በፊት በዚህ ክፍል ኤፍሬም ዓለሙን (ፍፁም ዓለሙ ተብሎ ስሙ ተቀይሯል) ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉ ሲሆን በቀጣይ ዓመት ጥሩ የአማካይ ክፍል ይኖራቸዋል ተብሎ ይገመታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ

በድረ-ገጻችን ላይ የሚወጡ ጽሁፎች ምንጭ ካልተጠቀሱ በቀር የሶከር ኢትዮጵያ ናቸው፡፡ እባክዎ መረጃዎቻችንን በሚጠቀሙበት ወቅት ምንጭ መጥቀስዎን አይዘንጉ፡፡