አስቻለው ግርማ ሰበታ ከተማን ተቀላቀለ 


ባለፉት ሦስት ቀናት በርካታ ተጫዋቾች አስፈርመው ሌሎች ትልልቅ ስም ያላቸው ተጫዋቾን ለማስፈረም እንቅስቃሴ እያደረጉ የሚገኙት ሰበታ ከተማዎች አስቻለው ግርማን አስፈርመዋል።

በ2005 ከሱሉልታ ከተማ ወደ ኢትዮጵያ ቡና አምርቶ በ2008 በሀዋሳ ከመጫወቱ በቀር ለቡና ግልጋሎትን የሰጠው የመስመር አጥቂው የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት በጅማ አባ ጅፋር ያሳለፈ ሲሆን በዚህ ዝውውር መስኮት ስሙ ከበርካታ የሊጉ ክለቦች ጋር እየተያያዘ ቢቆይም በሀዋሳ አብረውት ከሰሩት የቀድሞ አሰልጣኙ ውበቱ አባተ ስር በድጋሚ ለመስራት ወደ ሰበታ ከተማ አምርቷል።

ለሰበታ 10ኛ አዲስ ፈራሚ የሆነው አስቻለው በተከላካይ እና አማካይ ክፍል ላይ ላተኮረው የክለቡ የዝውውር እንቅስቃሴ በመስመር አጥቂ ሚና ላይ አማራጭ እንደሚፈጥር ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ