ወላይታ ድቻ የግራ መስመር ተከላካይ አስፈረመ

ወላይታ ድቻ ዘንድሮ በወልዲያ በግራ ተከላካይነት ስፍራ ሲጫወት የነበረው ይግረማቸው ተስፋዬን አስፈርሟል፡፡

ከቢሾፍቱ የተገኘውና በዱከም ከተማ የእግር ኳስ ህይወቱን የጀመረው ተጫዋቹ በ2010 ወደ ሀዲያ ሆሳዕና አምርቶም መጫወት የቻለ ሲሆን የተጠናቀቀውን የውድድር ዓመት ደግሞ ወደ ወልዲያ አምርቶ በግሉ የተሳካ ጊዜ ማሳለፍ ከቻለ በኋላ የፕሪምየር ሊጉ ክለብ ወላይታ ድቻን በሁለት ዓመት ውል ተቀላቅሏል፡፡

አማካዩ ሰለሞን ወዴሳን ለማስፈረም ተስማምተው ከገንዘብ ጋር በተያያዘ ለመልቀቅ እንደተገደዱ ለሶከር ኢትዮጵያ የገለፁት አሰልጣኝ ገብረክርስቶስ ቢራራ በቀጣዩ ቀናትም ወጣት ተጫዋቾችን ወደ ክለቡ ለማምጣት እንዳሰቡ የገለፁ ሲሆን መስከረም 5 የቅድመ ውድድር ዝግጅት እንደሚጀምሩም ገልፀውልናል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ