ድሬዳዋ ከተማ አምስተኛ ተጫዋች አስፈርሟል

ከትላንት በስቲያ ባስፈረሟቸው አራት ተጫዋቾች ወደ ዝውውር የገቡት ድሬዳዋ ከተማዎች ፍሬዘር ካሳን አምስተኛ ፈራሚ አድርገዋል።

ከቅዱስ ጊዮርጊስ የታዳጊ ቡድን የተገኘው እና ያለፉትን ሦስት ዓመታት በዋናው ቡድን ያሳለፈው ፍሬዘር በተለይ በ2009 ድንቅ ጊዜ ከቡድኑ ጋር ማሳለፍ ችሎ ነበር። በኦሊምፒክ ብሔራዊ ቡድንም ጨዋታዎችን አድርጓል። ሆኖም ያለፉትን ሁለት የውድድር ዘመናት በቂ የመሰለፍ ዕድል አለማግኘቱን ተከትሎ ክለቡን በመልቀቅ የአሰልጣኝ ስምዖን ዓባይን ክለብ ማረፊያውን አድርጓል፡፡

በቀኝ እና መሐል ተከላካይነት መጫወት የሚችለው ፍሬዘር ከሌላው ሁለገብ ዘሪሁን አንሼቦ እና የቀድሞ የቡድን ጓደኛው ዘካርያስ በመቀጠል በተከላካይ ስፍራ ላይ የፈረመ ሦስተኛው ተጫዋች ሆኗል።


© ሶከር ኢትዮጵያ