ከፍተኛ ሊግ | ቡታጅራ ተጨማሪ ተጫዋች አስፈርሟል

ቡታጅራ ከተማ በላይ ገዛኸኝን የክለቡ ዘጠነኛ ፈራሚ አድርጎ ወደ ቡድኑ ቀላቅሏል።

በላይ በአንደኛ ሊግ ውድድር ከባቱ ከተማ ጋር አሸናፊ በመሆን ወደ ከፍተኛ ሊግ እንዲያድግ ጉልህ ሚና የተጫወተ ሲሆን 10 ጎሎችን በማስቆጠርም የክለቡ ከፍተኛ ጎል አስቆጣሪ ሆኖ ያጠናቀቀ የአጥቂ መስመር ተሰላፊ ነው። ቡታጅራ ከተማ በክረምቱ ወደ ዲላ ከተማ የተዘዋወረውን ወሳኝ አጥቂ ክንዴ አብቹን በበላይ ይተካል ተብሎም ይጠበቃል።

በ2011 ላለመውረድ የተጫወተው ቡታጅራ ከተማ በዘንድሮ ዓመት ጠንካራ ተፎካካሪ ሆኖ ለመገኘት የአሰልጣኝ አሥራት አባተን ቅጥር በመፈፀም የ13 ተጨዋቾችን ውል ከማደሱ በተጨማሪ 9 አዲስ ተጨዋቾችን ማስፈረሙ ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ