ደቡብ ፖሊስ የአማካዩን ውል አራዘመ

ደቡብ ፖሊስ የተከላካይ አማካዩን ኤርሚያስ በላይን ውል አራዝሟል፡፡

ቢጫ ለባሾቹ በርካታ አዳዲስ ተጫዋቾችን በማስፈረም ወደ ቅድመ ውድድር ዝግጅት የገቡ ሲሆን አሁን ደግሞ የነባሮችንም ውል ማራዘም ጀምረዋል፡፡ የተከላካይ አማካዩ ኤርሚያስ በላይም ውሉን ካራዘሙ ተጫዋቾች ቀዳሚው ሆኗል፡፡

ከሀዋሳ ከተማ ታዳጊ ቡድን አንስቶ እስከ ዋናው መጫወት ከቻለ በኃላ በአርባምንጭ ከተማ እና ሰበታ ከተማ የተጫወተው ይህ አማካይ በ2011 በደቡብ ፖሊስ ጥሩ ጊዜ ማሳለፉን ተከትሎ ወደ ሌሎች ክለቦች ያመራል ተብሎ ቢጠበቅም በድጋሚ ለአንድ ዓመት ለመቆየት ፊርማውን አኑሯል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ