የፌዴሬሽኑ ሥራ አስፈፃሚ ነገ ስብሰባ ያደርጋል

አጠቃላይ የ2012 የውድድር ዘመን መቼ እንደሚጀምር ቁርጡ ባልታወቀበት በአሁኑ ጊዜ የፌዴሬሽኑ አመራሮች ነገ ስብሰባ ያደርጋሉ።

ከረፋዱ 04:00 ፌዴሬሽኑ አዲስ በገዛው ህንፃ ላይ በሚካሄደው በዚህ ስብሰባ በርከት ያሉ አጀንዳዎች ይነሳሉ ተብሎ ሲጠበቅ በዋናነት በወቅታዊው የእግርኳሱ ችግር ዙርያ የመፍትሔ አቅጣጫ ለመስጠት ባሳለፍነው ሳምንት በኢፌዲሪ ስፖርት ኮሚሽን ሰብሳቢነት በተካሄደው ውይይት እንዲሁም በቀጣይ ጥቅምት አንድ ይካሄዳል ተብሎ ቀጠሮ በተያዘለት ዓመታዊ ጠቅላላ ጉባኤ ዙርያ ሰፊ ጊዜ ወስደው ይነጋገራሉ ተብሎ ይጠበቃል።

ከነገው ስብሰባ አስቀድሞ አዳዲስ ነገሮች እየተሰሙ በሚገኝበት በአሁኑ ወቀት የፌዴሬሽኑ አመራሮች በቀጣዩ የእግርኳስ እጣ ፈንታ ዙርያ ምን ዓይነት ውሳኔ ያሳልፋሉ የሚለው ተጠባቂ ነው።


© ሶከር ኢትዮጵያ