ደደቢት የተከላከይ መስመር ተጫዋች አስፈረመ

በትናንትናው ዕለት የቅድመ ውድድር ዝግጅታቸውን የጀመሩት ደደቢቶች የግራ መስመር ተከላካዩ ዳዊት ዕቁበዝጊን አስፈርመዋል።

ያለፈውን የውድድር ዓመት በአክሱም ከተማ ያሳለፈው ተጫዋቹ ከዚህ ቀደም ወልዲያ እና መቐለ ወደ ፕሪምየር ሊጉ ሲያድጉ የቡድኖቹ አባል የነበረ ሲሆን ከአሰልጣኝ ጌታቸው ዳዊት ጋርም ለአራተኛ ጊዜ በድጋሚ የሚሰራ ይሆናል።

ከተጠቀሱት ክለቦች በተጨማሪ በወልዋሎ የተጫወተው የመስመር ተከላካዩ የደደቢት ስድስተኛ ፈራሚ ሲሆን የአሰልጣኙ ቀዳሚ ምርጫ ይሆናል ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ