የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ይካሄድ ይሆን ?

የ2011 የውድድር ዘመን የፕሪምየር ሊጉ ቻምፒዮን መቐለ 70 እንደርታ እና የኢትዮጵያ ዋንጫ አሸናፊው ፋሲል ከነማ መካከል የአሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ መቼ ይካሄድ ይሆን?

የፕሪምየር ሊጉ ዐቢይ ኮሚቴ ዛሬ ባደረገው የመጀመርያው ስብሰባ በዚህ ጨዋታ ዙርያ ምንም እንዳልተነጋገረ አረጋግጠናል። ይህ ውድድር አዲሱን የፕሪምየር ሊግ ኮሚቴን የማይመለከት እና በቀድሞ የሊግ ኮሚቴ የሚመራ በመሆኑ ጉዳዩን ሳይመለከቱት እንደቀሩ ሰምተናል።

ፌዴሬሽኑ በዚህ ውድድር ዙርያ ያሰበው ነገር ካለ ብለን ለማጣራት ያደረግነው ጥረት ለጊዜው ያልተሳካ ሲሆን የውድድሩ መካሄድ አለመካሄዱን አስመልክቶ በቀጣይ መረጃዎችን ካገኘን የምንመለስበት ይሆናል።

በፌዴሬሽኑ ትኩረት ማጣት በተለያዩ ጊዜያት አንዴ እየተካሄደ ሌላ ጊዜ ደግሞ ሳይካሄድ እየቀረ ሲቆራረጥ የቆየው የኢትዮጵያ አሸናፊዎች አሸናፊ ዋንጫ ጨዋታ ዘንድሮም የመካሄዱ ነገር አጠራጣሪ አድርጎታል።


© ሶከር ኢትዮጵያ