አራት ክለቦች ለጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ ድጋፍ አድርገዋል

እግሩ ላይ በገጠመው ህመም ህክምና ላይ ለሚገኘው ጋዜጠኛ ምስጋናው ታደሰ ኢትዮጵያ ቡና፣ ሰበታ ከተማ፣ ወልዋሎ እና ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ክለብ ድጋፍ አድርገዋል፡፡ 

ጋዜጠኛው ህመም ከገጠመው ጊዜ ጀምሮ በርካቶች ድጋፍ እያደረጉለት ሲሆን አሁንም ወደ ጤንነቱ በሰላም እንዲመለስ ሁሉም ርብርቡን ቀጥሏል፡፡ በዚህም መሠረት አራት ክለቦች ከተጫዋቾቻቸው በሰበሰቡት  የገንዘብ ድጋፍን አድርገዋል፡፡ ሰበታ ከተማ 10 ሺህ ብር፣ ኢትዮጵያ ቡና 15ሺህ ብር፣ ወልዋሎ 12ሺህ ብር እንዲሁም ኢትዮ-ኤሌክትሪክ ደግሞ 12 ሺህ ብር ለግሰዋል፡፡

ምስጋናውን ለመደገፍ ከታች ያሉትን አካውንቶች ይጠቀሙ፡-

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ – 1000268456639

አዋሽ ባንክ – 01320148371700

GO Fund Me – https://www.gofundme.com/f/hynuzf?utm_source=facebook&utm_medium=social&utm_campaign=p_cp+share-sheet


© ሶከር ኢትዮጵያ