ከፍተኛ ሊግ | የኢትዮጵያ መድን ተጫዋቾች በክለቡ ላይ ቅሬታ አቀረቡ

በ2011 ውድድር ዓመት ኢትዮጵያ መድን ሲያገለግሉ የነበሩ ተጫዋቾች ከደሞዝ ጋር በተያያዘ ያላቸውን ቅሬታ ለኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን አቀርበዋል።

ተጫዋቾቹ በቅሬታቸው “ከክለቡ ጋር ያለን ውል እስከ ነሐሴ 30 ድረስ እንደሚቆይ የሚታወቅ ቢሆንም ቡድኑ የሚገባንን የደሞዝ ክፍያ እስካሁን አልፈፀመልንም። በተጨማሪም ክስ ካላቋረጣችሁ መልቀቂያ አንሰጥም እየተባልን ነው።” በማለት ፌዴሬሽኑ ጉዳዩን አይቶ መፍትሄ እንዲሰጣቸው በደብዳቤ ጠይቀዋል።

የቅሬታ ደብዳቤው ይህን ይመስላል፡-


© ሶከር ኢትዮጵያ