ትውልደ ኢትዮጵያዊው ለአደላይድ ዩናይትድ የመጀመርያ ጨዋታውን አደረገ

ትውልደ ኢትዮጵያዊው የመስመር ተከላካይ ያሬድ አብው ለአውስትራሊያው አደላይድ ዩናይትድ የመጀመርያ ጨዋታውን አድርጓል።

በአውስትራሊያ ትልቁ ሊግ (ኤ-ሊግ) ትናንትናው ዕለት አደላይድ ከሜዳው ውጪ በሜልቦርን ሲቲ 2-1 በተሸነፉበት ጨዋታ የመጀመርያ ጨዋታውን ያደረገው ይህ የ20 ዓመት ተጫዋች ተስፋ ሰጪ እንቅስቃሴ ቢያሳይም ከዕረፍት በፊት በገጠመው ጉዳት ተቀይሮ ከሜዳ ወጥቷል።

ኃይት ሲቲ ከተባለ የወጣቶች ቡድን አድጎ በናሽናል ፕሪምየር ሊግ ተሳታፊው ኩሮይዶን ኪንግስ ያመራው ያሬድ ባለፈው ዓመት ነበር የአደላይድ ከ23 ዓመት በታች ቡድን የተቀላቀለው።

በአሰልጣኝ ገርትጃን ቫርበክ እየተመሩ ሁለት ተከታታይ ጨዋታዎች ተሸንፈው መጥፎ አጀማማር ያደረጉት አደላይዶች በቀጣይ ሳምንት ኒውካስትል ዩናይትድ ጄትስን ይገጥማሉ።


© ሶከር ኢትዮጵያ