የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት የሚካሄድበት ቀን ታውቋል

ጥቅምት 22 ለሚጀመረው የአዲስ አበባ ከተማ ዋንጫ ቀጣይ ሐሙስ 3:30 በመዘጋጃ ቤት አዳራሽ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ይካሄዳል።

ስምንት ቡድኖች የሚያሳትፈው ይህ ውድድር ዘንድሮ ለ14ኛ ጊዜ የሚካሄድ ሲሆን ሁለቱ የከተማው ትላልቅ ክለቦችን ጨምሮ መከላከያ፣ ኤሌክትሪክ፣ ወልዋሎ፣ ሰበታ፣ ወልቂጤ እና ባህር ዳር ከተማ እንደሚያሳትፍ ሲረጋገጥ በዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓቱም የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አቶ ታከለ ኡማ (ኢንጂነር) እንደሚገኙ ታውቋል።

ከወዲሁ ጠንካራ ፉክክር ይታይበታል ተብሎ የሚጠበቀው ይህ ውድድር በአዲስ ቴሌቭዥን በቀጥታ የሚተላለፍ ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ