ካሜሩን 2021 | ኢትዮጵያ ከሜዳዋ ውጪ ማዳጋስካርን ነገ ትገጥማለች

በካሜሩን አዘጋጅነት ለሚደረገው የ2021 የአፍሪካ ዋንጫ የማጣሪያ ጨዋታን በዚህ ሳምንት ማድረግ የሚጀምሩ ሲሆን ኢትዮጵያም ነገ ከሜዳዋ ውጪ ማዳጋስካርን አንታናናሪቮ ላይ ትገጥማለች፡፡

በምድብ 11 ከኒጀር፣ አይቮሪኮስት እና ማዳጋስካር ጋር የተደለደለው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ወደ ስፍራው ሀያ ተጫዋቾች በመያዝ ከሶስት ቀናት በፊት ቀደም ብሎ ያመራ ሲሆን በቡድኑ ውስጥ ሁሉም ተጫዋቾች ከጉዳት ነፃ ሆኖ የነገውን ጨዋታ እየተጠባበቀ እንደሚገኝ አሰልጣኙ በስፍራው ለጋዜጠኞች በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ አረጋግጠዋል፡፡

አሰልጣኙ አክለውም “ወደዚህ የመጣነው ሶስት ነጥብን ፈልገን ነው። ያን ለማድረግ ደግሞ ዝግጁ ነን።” ያሉ ሲሆን በቆይታቸውም የመለማመጃ ሜዳው እና ሆቴሉ በአቅራቢያው መገኘቱም ምቾትን እንደፈጠረላቸው ገልፀዋል፡፡ ዛሬ አመሻሽ ቡድኑ የመጨረሻ ልምምዱን ያከናወነ ሲሆን ነገ 10:00 ሰአት 22 ሺህ ተመልካቾችን መያዝ በሚችለው ማሃማሲና ሙኒሲፓል የመጀመሪያውን የነጥብ ጨዋታ ያደርጋል።


© ሶከር ኢትዮጵያ