የፕሪምየር ሊጉ ዕጣ ድልድል ይፋ ሆኗል

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ዛሬ በአዳማ ሲደረግ ክለቦችም ተጋጣሚዎቻቸውን አውቀዋል።

የ2012 የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ኅዳር 21 እንደሚጀመር ዛሬ ከሰዓት በአዳማ ኤክስኪውቲቭ ሆቴል እየተደረገ ባለው የዕጣ ማውጣት ስነስርአት የተገለፀ ሲሆን የመጀመሪያው ሳምንት የሊጉ መርሃግብርም በዕጣ ከተለየ በኋላ እንደሚከተለው ይፋ ሆኗል፡፡

አዳማ ከተማ ከ ፋሲል ከተማ
ወልቂጤ ከተማ ከ ቅዱስ ጊዮርጊስ
ሰበታ ከተማ ከ ወልዋሎ ዓዲግራት ዩ.
ወላይታ ድቻ ከ ሲዳማ ቡና
ስሑል ሽረ ከ ኢትዮጵያ ቡና
ጅማ አባ ጅፋር ከ ባህርዳር ከተማ
መቐለ 70 እንደርታ ከ ሀድያ ሆሳዕና
ሀዋሳ ከተማ ከ ድሬዳዋ ከተማ

*ቅድሚያ የተፃፉት ባለሜዳ ናቸው

የውድድሩን ሙሉ መርሐ ግብር ከቆይታ በኋላ ይዘን እንመለሳለን


© ሶከር ኢትዮጵያ