ኮትዲቯርን የሚገጥመው የዋሊያዎቹ 11 ተሰላፊዎች ታውቀዋል

አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ኮትዲቯርን የሚገጥምላቸውን የመጀመርያ 11 መርጠዋል።

ቡድኑ ባሳለፍነው እሁድ ማዳጋስካርን ከገጠመው ስብስብ የሁለት ተጫዋቾች ለውጥ ያደረገ ሲሆን በአማካይ ስፍራ ታፈሰ ሰለሞን በጋቶች ፓኖም ምትክ፣ በአጥቂ ስፍራ ላይ አዲስ ግደይ በአማኑኤል ገብረሚካኤል ምትክ የመጀመርያ አሰላለፉ ላይ ተካተዋል።

በወረቀት ላይ ሲታይ የማጥቃት ባህርይ ባላቸው ተጫዋቾች የተዋቀረው የመጀመርያ አሰላለፍ ይህን ይመስላል

አቤል ማሞ

አህመድ ረሺድ – አስቻለው ታመነ – አንተነህ ተስፋዬ – ረመዳን የሱፍ

ታፈሰ ሰለሞን – ይሁን እንደሻው – ሽመልስ በቀለ

ሱራፌል ዳኛቸው – አዲስ ግደይ – አቡበከር ናስር


© ሶከር ኢትዮጵያ