ድሬዳዋ ከተማ አዲስ ሥራ አስኪያጅ ሾመ

ለ2012 የውድድር ዘመን ራሱን እያዘጋጀ የሚገኘው ድሬዳዋ ከተማ አዲስ ሥራ አስኪያጅ መሾሙን አስታውቋል።

ያለፉትን ኹለት ዓመታት ክለቡን በሥራ አስኪያጅነት ሲያገለግሉ የቆዩት አቶ አንበስ አጉቾን በማንሳት የክለቡ ቦርድ አመራር በዛሬው ዕለት አቶ ፍፁም ክንድሼን አዲሱ ሥራ አስኪያጅ አድርጎ መሾሙን በደብዳቤ አረጋግጧል።

አቶ ፍፁም ከዚህ ቀደም ክለብ ውስጥ በህዝብ ግኑኝነት እና በማርኬት ክፍል ውስጥ ሲሰሩ የቆዩ ሲሆን በተለይ በህዝብ ግንኙነት ሥራቸው የክለቡን አጠቃላይ እንቅስቃሴ ሰድሮ በማዘጋጀት መረጃዎችን በትጋት ሲያደርሱ መቆየታቸው ይታወቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ