መቐለዎች የመጀመርያው ሳምንት ጨዋታቸውን በዝግ ያካሂዳሉ

መቐለዎች የ2012 የመጀመርያ የፕሪምየር ሊግ ጨዋታቸውን በዝግ ያካሂዳሉ።

ባለፈው ዓመት ፋሲል ከነማ እና ደደቢትን ባገናኘው ጨዋታ በተፈጠረው ክስተት አንድ ጨዋታ በዝግ እንዲያካሂዱ የተወሰነባቸው መቐለዎች ባለፈው ዓመት በይግባኝ ያደረላቸው ውሳኔ በዚህ ዓመት ተግባራዊ ይሆናል።

በወቅቱ አነጋጋሪ በነበረው እና ፋሲል ከነማ በሰፊው ውጤት ባሸነፈበት ጨዋታ በሜዳ ውስጥ የመቐለ መለያ የለበሱ ደጋፊዎች በተጋጣሚ ቡድን ላይ ጥቃት አድርሰዋል በሚል ቡድኑ ላይ ቅጣት እንደተጣለ ይታወሳል።

በዚህም መሠረት የዐምናው ቻምፒዮን መቐለ በመጀመርያው ሳምንት አዲስ አዳጊው ሀዲያ ሆሳዕናን የሚገጥምበት ጨዋታ በዝግ ስታዲየም የሚከናወን ይሆናል።


© ሶከር ኢትዮጵያ