ጅማ አባ ጅፋሮች የመጀመርያ ጨዋታቸውን ከሜዳ ውጭ ያደርጋሉ

ጅማ አባጅፋሮች በሜዳቸው ከባህር ዳር ከተማ ጋር እንዲያደርጉ መርሐ ግብር ቢወጣላቸውም ከባለፈው ዓመት በተሸጋገረ ቅጣት ምክንያት መጀመርያ ሳምንት የሊጉ ጨዋታቸውን ከሜዳቸው ውጭ ያደርጋሉ።

ባሳለፍነው ዓመት በ26ኛው ሳምንት ከመቐለ 70 እንደርታ ጋር በነበረው ጨዋታ በተፈጠረ የዲሲፕሊን ጥሰት ኹለት ጨዋታ ከሜዳ ውጭ እንዲጫወት እና 100,000 ብር ቅጣት ተላልፎበት እንደነበረ ይታወቃል። ሆኖም ክለቡ ባቀረበው ይግባኝ መሠረት ጉዳዩ በድጋሚ እስኪታይ ድረስ በ28ኛው እና 30ኛው ሳምንት ከኢትዮጵያ ቡና እና ከደቡብ ፖሊስ ጋር ባደረጋቸው የሜዳው ጨዋታዎች ቅጣቱ ተግባራዊ ሳይደረግ ለተመልካች ክፍት ሆኖ መጫወቱ ይታወሳል።

የውድድሩ ዐቢይ ኮሚቴ ጉዳዩን ተመልክቶ በወሰነው ውሳኔ ቅጣቱ የፀና ሲሆን በዚህም መሠረት በሜዳው ከባህር ዳር ከተማ ጋር መጫወት የሚገባውን የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታ ሰኞ ኅዳር 22 ቀን 2012 በአዳማ ከተማ እንዲያከናውን ከውሳኔ ተደርሷል።


© ሶከር ኢትዮጵያ