ኡመድ ዑኩሪ ግብ አስቆጥሯል

በውድድር ዓመቱ መጀመርያ አስዋንን የተቀላቀለው ኡመድ ኡክሪ ዛሬ በተደረገ የግብፅ ፕሪምየር ሊግ ጨዋታ ሁለት ግቦች አስቆጥሯል።

በስድስተኛ ሳምንት የግብፅ ፕሪምየር ሊግ አዲስ አዳጊው አስዋን ከሜዳው ውጭ ከሊጉ መሪ ፒራሚድስ ጋር ሁለት ለሁለት በተለያየበት ጨዋታ ነው ኢትዮጵያዊው አጥቂ ሁለት ግቦች ያስቆጠረው። በጨዋታው በአንቲዊ እና ሰላማ ግቦች በሁለት አጋጣሚዎች ሲመሩ የቆዩት አስዋኖች በዑመድ ኡክሪ ሁለት ወሳኝ ግቦች አቻ ተለያይተው ከወራጅ ቀጠናው መውጣት ችለዋል።

አስዋኖች በስድስት ጨዋታዎች አምስት ነጥቦች ሰብስበው በአስራ አራተኛ ደረጃ ላይ ሲቀመጡ በቀጣይ ጨዋታ ኡመድ ኡክሪ በግብፅ ቆይታው ጥሩ ብቃት ያሳየበትን ኤል ኢንታግ ኤል ሐርቢን ይገጥማል።


© ሶከር ኢትዮጵያ