የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን የኮከቦች ሽልማት የሚካሄድበት ቀን ታወቀ

የመካሄድ ነገሩ ጥያቄ ውስጥ ገብቶ የነበረው የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን የኮከቦች ሽልማት በቀጣይ ሳምንት እንደሚካሄድ ታውቋል።

የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን ጥላ ስር በሚካሄዱት ውድድሮች ላይ የላቀ እንቅስቃሴ ላደረጉ አካላት እውቅና የሚሰጥበት ይህ መርሐ ግብር በመጪው ህዳር 27 በስካይ ላይት ሆቴል የሚካሄድ ይሆናል።

ከፌደሬሽኑ ጠቅላላ ጉባዔ አንድ ቀን ቀደም ብሎ በሚደረገው በዚህ መርሐግብር በርካታ የተለዩ ነገሮች ሊኖሩ ይችላሉ ተብሎ ይጠበቃል።


© ሶከር ኢትዮጵያ