ከፍተኛ ሊግ | ደቡብ ፖሊስ አራት ተጫዋቾችን አስፈረመ

በአሰልጣኝ ተመስገን ዳና እየተመራ ነባር እና አዳዲሶቹ ተጫዋቾችን በመያዝ ለወራት ዝግጅቱን ሲሰራ የቆየው ደቡብ ፖሊስ ተጨማሪ አራት አዳዲስ ተጫዋቾችን አስፈርሟል፡፡

ከአሰልጣኝ ተመስገን ዳና ጋር ከዚህ በፊት በሀዋሳ ከ17 እና 20 ዓመት በታች ቡድን ውስጥ አምበል በመሆን ሲጫወት የነበረው የግራ መስመር ተከላካዩ ጌታሁን አየለ ከቀድሞው አሰልጣኙ ጋር ዳግም ለመስራት ወጣቱ ተከላካይ ቡድኑን ተቀላቅሏል፡፡

በወልቂጤ እና አምና ደግሞ በካፋ ቡና በመጫወት ያሳለፈው የአማካይ ስፍራ ተጫዋች ካሳሁን ገብረሚካኤል ሌላኛው የቡድኑ ፈራሚ ሲሆን ዐምና በአርባምንጭ ከተማ ቆይታን ያደረገው አማካዩ ብሩክ ዋኮ እንዲሁም የቀድሞው የስልጤ ወራቤ ግብ ጠባቂ ሞላ ክፍሉ ክለቡን የተቀላቀሉ ወጣት ተጫዋቾች ሆነዋል፡፡


© ሶከር ኢትዮጵያ