የ2012 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ዓመታዊ ስብሰባ እና የዕጣ ማውጣት ሥነ-ስርዓት ተከናወነ

የ2011 የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ ክለቦች ዓመታዊ ስብሰባና የ2012 የውድድር ዘመን የእጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ዛሬ ረፋድ በጁፒተር ሆቴል ተካሂዷል።

ዝግጅቱን በመክፈቻ ንግግር የከፈቱት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌደሬሽን ፕሬዝዳንት አቶ ኢሳይያስ ጅራ በንግግራቸው የከፍተኛ ሊግ ውድድር ከነበረበት ደረጃ ከፍ ለማድረግ በኃላፊነት መስራት እንዳለባቸው ገልፀው ስፖርቱን ለሰላማዊ ግንኙነት መጠቀም እንደሚገባ አሳስበዋል። ባለፈው ዓመት በአንዳንድ ቦታዎች የተከሰቱት ችግሮች በዘንድሮ ውድድር ዓመት እንዳይከሰቱ ጠንክሮ መስራት እነሰደሚገባም ገልፀዋል። “ሁላችሁም ወደ ምትሄዱበት ቦታ የሰላም አምባሳደር መሆን አለባችሁ።” ሲሉም መልዕክት አስተላልፈዋል።

በመቀጠል ከከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አቶ ስንታየው ወልደማርያም የ2011 የውድድር ዘመን አፈፃፀም ሪፖርት እንዲሁም አቶ ፍቃዱ ጥላሁን ከብሔራዊ ዳኞች ኮሚቴ የ2011 ውድድር ዓመት የዳኝነት አፈፃፀም ሪፖርት ለተሰብሳቢዎች ቀርቧል።

መርሃግብሩ ከሻይ እረፍት መልስ በማስከትል የ2012 የውድድር ደንብ የከፍተኛ ሊግ ኮሚቴ አባል አቶ ኃይሉ ምህረትአብ አማካይነት ቀርቧል ፤ የ2012 የምድብ ድልድል እንዴት በምን መልክ ተመደቡ የሚለውን በኮሚቴው ምክትል ሰብሳቢ በሆኑት ሻምበል ሀለፎም ቀርቧል። በመቀጠል ከተሳታፊዎች በቀሩቡት ሪፖርቶችና በቀጣይ ውድድሩ በምን መልክ መካሄድ አለበት በሚሉ ጉዳዮች ላይ በርካታ ሀሳቦች ተሰጥተዋል። በሊጉ የሚዲያ ትኩረት ማጣት፣ መውጣት መውረድ ጉዳይ ፤ የውድድሩ የቅርፅ ለውጥ፣ የምድብ ድልድል አወጣጥና ሌሎች በርካታ ጉዳዩች የተነሱ ሲሆን የሚመለከታቸው የስራ ኃላፊዎች ምላሽ ሰጥተዋል።

በመጨረሻም የዕጣ ማውጣት ስነ-ስርዓት ከመካሄዱ በፊት ፌዴሬሽኑ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል፤ በፊት በነበረው ድልድል የወረዱት እና ወደላይ የወጡት ብቻ በየምድቡ ይግቡ እና እንዳአዲስ እጣ ይውጣ የሚል የሀሳብ ክርክር ተደርጦ በድጋሚ እጣ ይውጣ የሚለው ውድቅ ሆኞ በስተመጨረሻ ፌዴሬሽኑ አስቀድሞ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል ወይም በፊት በነበረው ድልድል የወረዱት እና ወደላይ የወጡት ብቻ በየምድቡ ይግቡ የሚለው ሀሳቦች ለቤቱ ድምፅ እንዲሰጡ የተደረገ ሲሆን በድምፅ አሰጣጡ ወቅት የነበረው ስርአት አልባ እንቅስቃሴ ስብሰባውን ሲያውክ ተስተውሎል። በስተመጨረሻም በድምፅ ብልጫ 27 ለ9 በሆነ ውጤት ፌዴሬሽኑ ባወጣው ምድብ ድልድል እንቀጥል የሚለው ሀሳብ ፀድቋል።

በዚህም መሠረት የኢትዮጽያ ከፍተኛ ሊግ ምድቦች የሚከተሉት ሆነዋል፡-


ምድብ ሀ

ደደቢት
ሶሎዳ ዓድዋ
ሰሜንሸዋ ደብረብርሃን
አክሱም ከተማ
ለገጣፎ ለገዳዲ
ኢትዮ ኤሌክትሪክ
ደሴ ከተማ
ፌዴራል ፖሊስ
ገላን ከተማ
አቃቂ ቃሊቲ
ወልዲያ
ወሎ ኮምቦልቻ

የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች

ለገጣፎ ከ ደሴ ከተማ
አክሱም ከተማ ከ ደብር ብርሃን
ገላን ከተማ ከ ሶሎዳ አድዎ
ወልዲያ ከ ፌዴራል ፖሊስ
ደደቢት ከ ኤሌክትሪክ
ወሎ ኮምበልቻ ከ አቃቂ ቃሊቲ

ምድብ ለ

መከላከያ
ሻሸመኔ ከተማ
ኢኮስኮ
ሀላባ ከተማ
ቤንች ማጅ ቡና
ጅማ አባቡና
ነቀምት ከተማ
አዲስ አበባ ከተማ
ጋሞ ጨንቻ
ካፋ ቡና
ወላይታ ሶዶ
ሀምበርቾ

የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች

ወላይታ ሶዶ ከ አምበሪቾ
ከፋ ቡና ከ ቤንች ማጂ ቡና
ሻሸመኔ ከ ጋሞ ጨንቻ
አዲስ አበባ ከ መከላካያ
ነቀምት ከ ሀላባ ከተማ
ኢኮስኮ ከ ጅማ አባቡና

ምድብ ሐ

ደቡብ ፖሊስ
ኢትዮጵያ መድን
ባቱ ከተማ
ጌዴኦ ዲላ
አርባምንጭ ከተማ
ስልጤ ወራቤ
ከምባታ ሺንሺቾ
ቡታጅራ ከተማ
የካ ክፍለ ከተማ
አርሲ ነገሌ
ኮልፌ ቀራንዮ
ቂርቆስ ክ/ከተማ

የመጀመርያ ሳምንት ጨዋታዎች

ቂርቆስ ክፍለ ከተማ ከ ኢትዮጵያ መድን
ኮልፌ ክፍለ ከተማ ከ አርባምንጭ
የካ ክፍለ ከተማ ባቱ ከተማ
ቡታጅራ ከ ደቡብ ፖሊስ
አርሲ ነገሌ ከ ዲላ ከተማ
ሺንሺቾ ከ ስልጤ ወራቤ


© ሶከር ኢትዮጵያ