የኢትዮጵያ ከፍተኛ ሊግ 5ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በተለያዩ የክልል ከተሞች ይደረጋሉ፡፡
በምድብ ሀ መሪው ወልድያ ወደ ባህርዳር ተጉዞ እሁድ አማራ ውሃ ስራን ሲገጥም ተከታዩ አአ ፖሊስ ቅዳሜ አበበ ቢቂላ ላይ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርትን ይገጥማል፡፡ እስካሁን በራሱ ሜዳ ጨዋታ ማድረግ ያልቻለው ሱሉልታ ከተማ መቐለ ከተማን በሚያስተናግድበት ጨዋታ ለመጀመርያ ጊዜ ሱሉልታ ላይ ይጫወታል፡፡
የምድብ ሀ የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር የሚከተለው ነው፡-
በምድብ ለ የሳምንቱ ተጠባቂ ጨዋታ ጅማ ላይ ይካሄዳል፡፡ ጨዋታውን ለመዘገብ ሶከር ኢትዮጵያ ወደ ስፍራው የምታቀና ሲሆን በ12 ነጥብ የምድቡ አናት ላይ የተቀመጠው አአ ከተማ 8 ነጥ ከያዘው ጅማ አባ ቡና ጋር ከባድ ፍልሚያ ያደርጋሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ 2ኛ ደረጃ ላይ የተቀመጠው ሻሸመኔ ከተማ ወደ ባቱ ሲያመራ ያለፈውን ሳምንት ከፍተኛ ውጤት ያስመዘገበው ወራቤ ከተማ ወደ አርሲ ነገሌ ያቀናል፡፡
የምድብ ለ የዚህ ሳምንት መርሃ ግብር እንደሚከተለው ነው፡-
ፎቶ – የምድብ ሀ የደረጃ ሰንጠረዥን የሚመራው ወልድያ