የአሰልጣኞች አስተያየት | ፋሲል ከነማ 5-0 ድሬዳዋ ከተማ

ፋሲል ከነማ በሜዳው ድሬዳዋ ከተማን 5-0 ከሸነፈ በኋላ የፋሲል ዋና አሰልጣኝ ሥዩም ከበደ እንደሚከተለው አስተያየታቸውን ሰጥተዋል።

“ትልቁ ጥቅማችን ሜዳችን ምቹ መሆኑ ነው።”

“ከአሸናፊዎች አሸናፊ ጀምሮ አመጣጣችን በጣም ጥሩ ነው። አዳማም ያደረግነው ጨዋታ እንደዚህ በውጤት ባይደምቅም መልካም ነው። ከሜዳ ውጪ ነጥብ ይዘን መምጣታችን እንደመጀመሪያ ጨዋታ አይከፋም። በሜዳችን 15 ጨዋታ አለን ። ያቀድነው የሜዳችንን ጥቅም አስጠብቀን ማሸነፍ ነው ፤ ለዋንጫም ነው የምንጫወተው። ስለዚህ የሜዳችንን ጥቅም በአግባቡ እንጠቀማለን።”

” የዛሬው ጨዋታ በመጀመሪያው አጋማሽ ትንሽ የሚስተካከል ነገር ነበር። ሆኖም በሁለተኛው አጋማሽ ሙሉ በሙሉ ጥሩ ነው። ያገኘነው ነጥብም የበለጠ እንድንሰራ ያደርገናል። ”

“ትልቁ ጥቅማችን ሜዳችን ምቹ መሆኑ ነው። በዚህም በሜዳችን ከዚህ ወርቅ ደጋፊ ጋር ታጅበን አጠቃላይ ውድድሮችን በውጤት መጠቀም አለብን። ከሜዳ ውጪም ሲኖረንም የተሻለ ሜዳ ካገኘን ቡድናችን ኳስን ይዞ በጥሩ መልኩ መጫወት ስለሚችል መልካም ውጤት እናመጣለን። በአጠቃላይ የዛሬው ውሏችን ጥሩ ነበር። ደጋፊውንም ላመሰግን እወዳለሁ።”

* የድሬዳዋ ከተማው ምክትል አሰልጣኝ ፍስሀ ጥዑመልሳን አስተያየትን ማካተት አልቻልንም።


© ሶከር ኢትዮጵያ