ላልታወቀ ጊዜ የተራዘመው ፕሪምየር ሊግ የዝውውር መስኮቱ ዛሬ ይዘጋል

የ2012 የውድድር ዘመን በመጀመርያው ዙር ወቅት ከነበራቸው ድክመትምና ጥንካሬም በመነሳት በሁለተኛው ዙር የተሻለ ቡድን ይዘው ለመቅረብ ክለቦች ለአንድ ወር ያህል ሲያካሂዱት የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ የተጫዋቾች የዝውውር መስኮት ዛሬ ማምሻውን የሚዘጋ ይሆናል።

የካቲት 16 ተከፍቶ በነበረው የዝውውር መስኮት ምንም አይነት ተሳትፎ ባለማድረግ ቅዱስ ጊዮርጊስ፣ ኢትዮጵያ ቡና፣ ፋሲል ከነማ እና አዳማ ከተማ ተጠቃሽ ቡድኖች ናቸው። የተቀሩት አስራ ሁለት ቡድኖች ይነስም ይብዛም በዝውውሩ ላይ ተሳታፊ የነበሩ ሲሆን የመውረድ ስጋት ያለባቸው እንደ ወልዋሎ፣ ድሬዳዋ ከተማ እና ሀዲያ ሆሳዕና እንዲሁም ወገብ ላይ የሚገኘው ስሑል ሽረ በርከት ያሉ ተጫዋቾችን ወደ ቡድናቸው የቀላቀሉ ሆነዋል።

በሀገራችን በተከሰተው የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስጋት ምክንያት የኢትዮጵያ እግርኳስ ፌዴሬሽን እና የፕሪምየር ሊግ ኩባንያ ትናንት በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ሊጉን ጨምሮ በኢትዮጵያ የሚደረጉ የእግርኳስ ውድድሮች ላልታወቀ ጊዜ መራዘማቸውን ማሳወቃቸው ይታወቃል።

© ሶከር ኢትዮጵያ