ስሑል ሽረ አማካይ አስፈርሟል

በዚህ የዝውውር መስኮት ከወልቂጤ ከተማ ጋር በስምምነት የተለያየው በቃሉ ገነነ አምስተኛ የስሑል ሽረ ፈራሚ ሆኗል።

ከበርካታ አማካዮች ጋር የተለያዩት እና ከዚህ ቀደም አስራት መገርሳን አስፈርመው የአማካይ አማራጮቻቸው ለማስፋት ጥረት ያደረጉት ስሑል ሽረዎች አሁን ደግሞ በቃሉ ገነነን በማስፈረም በቦታው ያላቸውን የተገደበ አማራጭ አስፍተዋል።

በዝውውር መስኮቱ አስራት መገርሳ፣ ደስታ ጊቻሞ፣ ዮናታን ከበደ እና ጋናዊው ራሂም ኦስማኑ ያስፈረሙት ስሑል ሽረዎች ከአክሊሉ ዋለልኝ ፣ ሙላለም ረጋሳ፣ መድሀኔ ብርኃኔ እና ኃይልአብ ኃይለሥላሴ ጋር በስምምነት መለያየታቸው ይታወሳል።

© ሶከር ኢትዮጵያ